Shape

“ተሕሪፍ” تَحْرِيف

“ተሕሪፍ” تَحْرِيف

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

1-ተሕሪፍ ምን ማለት ነው ?
2-ቁርዓን ስለ ተሕሪፍ ምን ይላል ?
3-ነቢያችን ስለ ብርዘት ምን አሉ ?
4-ቀደምት ሙስሊም ሊቃውንት ስለ ተሕሪፍ ምን ይላሉ ?

1⃣ “ተሕሪፍ” تَحْرِيف ማለት “ብርዘት” ማለት ሲሆን የቃለትን ብርዘት “Textual corruption” ያሳያል “ሐርፍ”حرف ማለት በራሱ “ፊደል” ማለት ነው።

The original meaning of the word Tahreef is “to lean from the pen in a certain direction” or ‘to twist words to correspond to one’s own desire
“ተሕሪፍ” ለሚለው ቃል ትክክለኛ ትርጉሙ “በብዕር አንድን ቃል ወደ ሌላ አቅጣጫ ዘንበል ማድረግ ወይም “ከራስ ፍላጎት ጋር እንዲሄድ ቃልን ማጣመም ማለት ነው”
[አል-ራጊቡ አል-ኢስፋሀኒ፣ አልሙፍረዳት ፊ ገሪብ አል-ቁርዓን 1995: ቅፅ 1 ገፅ 122]

Ash Shahrastani remarked that Tahreef means “changing the written word to an alternative to give it a corrupted meaning.
አሽ-ሻራስታኒ እንዳስቀመጠው ታሕሪፍ ማለት “የተፃፈውን ቃል ወደ ሌላ በመለወጥ የተዛባ ትርጉም እንዲኖረው ማድረግ ማለት ነው።
[አሽ-ሻራስታኒ ቅፅ 3 ገፅ 11]

ይህን እንደዚህ ከተረዳን የመጨረሻው ኪዳን የሆነው የአምላካችን አላህ ቅዱስ ቃል (ቁርዓን) ስለ “ተሕሪፍ” ምን ይላል የሚለውን ከብዙ ጥቂቱን ብቻ እንመልከት።

2⃣ ቁርዓን ስለ ብርዘት “Corruption” ምን ይላል ?

فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ الْكِتَابَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ فَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ
ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው።
ሁለን ፈጣሪ በሆነው በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩሕ በጣም አዛኝ በሆነው።
[Qur’an 2:79]

فَبِمَا نَقْضِهِم مِّيثَاقَهُمْ لَعَنَّاهُمْ وَجَعَلْنَا قُلُوبَهُمْ قَاسِيَةً ۖ يُحَرِّفُونَ الْكَلِمَ عَن مَّوَاضِعِهِ…
ቃል ኪዳናቸውንም በማፍረሳቸው ረገምናቸው፡፡ ልቦቻቸውንም ደረቆች አደረግን፡፡ ቃላትን ከቦታዎቻቸው ይለውጣሉ…
[Qur’an 5:13]

يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
«የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ»
[Qur’an 3:71]

۞ أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُونَ
(አይሁዶች) ከነሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት ሲኾኑ ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?
[Qur’an 2:75]

በእነዚህ የዘረዘርናቸው አናቅጽ ላይ “የሚለውጡት” ለሚለው ቃል የገባው “ዩሀሪፉነሁ” يُحَرِّفُونَهُ የሚል ሲሆን “የሚበርዙት” የሚል ትርጉም ይሰጠናል። የሚበርዙት ደግሞ “ሐርፍ” حَرْف “ፊደል” ሲሆን ፁሁፋዊ ብርዘትን “Textual Corruption” ያሳያል ይህም “ተሕሪፍ” ይባላል።

3⃣ የአላህ መልዕክተኛ ስለ ብርዘት ምን አሉ ?Prophet Mohammed About corruption.

عن أبي موسى قال : قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم – : ” إن بني إسرائيل كتبوا كتابا فاتبعوه ، وتركوا التوراة
The Messenger of Allah (ﷺ) said:The Bani Israel wrote a book, they followed it and left the Torah.
[አል-ጠበራኒ ሲልሲለ ሰሂሐ 2832]

በዚህ ሐዲስ ላይ በግልጽ የምንረዳው እስራኤላውያን ከአላህ የወረደውን መፅሐፍ ትተው የራሳቸው የሆነን መፅሐፍ እንደ ፃፉና በዚያ ሲመሩ እንደነበር ነው።

Comment (1)

  • MUHAMADJAMAL ALO ABDO

    May 30, 2024

    Maashaa allaah! Barnoota guddaadha.

Your email address will not be published. Required fields are marked*